Nehemiah 12

ካህናትና ሌዋውያን

1ከሰላትያል ልጅ ከዘሩባቤልና ከኢያሱ ጋር የተመለሱት ካህናትና ሌዋውያን እነዚህ ነበሩ፤

ሠራያ፣ ኤርምያስ፣ ዕዝራ፣
2አማርያ፣ መሉክ፣ ሐጡስ፣
3ሴኬንያ፣ ሬሁም፣ ሜሪሞት፣
4አዶ፣ ጌንቶን፣ አብያ፣
5ሚያሚን፣ መዓድያ፣ ቢልጋ፣
6ሸማያ፣ ዮያሪብ፣ ዮዳኤ፣
7ሰሉ፣ ዓሞቅ፣ ኬልቅያስና ዮዳኤ።

እነዚህ በኢያሱ ዘመን የካህናቱና የወንድሞቻቸው አለቆች ነበሩ።

8ሌዋውያኑ ደግሞ ኢያሱ፣ ቢንዊ፣ ቀድምኤል፣ ሰራብያ፣ ይሁዳ እንዲሁም ከወንድሞቹ ጋር የምስጋና መዝሙር ኀላፊ የሆነው መታንያ ነበሩ። 9ወንድሞቻቸው የሆኑት በቅቡቅያና ዑኒም በአገልግሎት ጊዜ ከእነርሱ ትይዩ ይቆሙ ነበር።

10ኢያሱ ዮአቂምን ወለደ፤
ዮአቂም ኤልያሴብን ወለደ፤
ኤልያሴብ ዮአዳን ወለደ፤
11ዮአዳ ዮናታንን ወለደ፤
ዮናታንም ያዱአን ወለደ።

12በዮአቂም ዘመን የካህናቱ ቤተ ሰብ አለቆች እነዚህ ነበሩ፤

ከሠራያ ቤተ ሰብ፣ ምራያ፤
ከኤርምያስ፣ ሐናንያ፤
13ከዕዝራ፣ ሜሱላም፤
ከአማርያ፣ ይሆሐናን፤
14ከሙሊኪ፣ ዮናታን፤
ከሰብንያ፣ ዮሴፍ፤
15ከካሪም፣ ዓድና፤
ከመራዮት፣ ሔልቃይ፤
16ከአዶ፣ ዘካርያስ፤
ከጌንቶን፣ ሜሱላም፤
17ከአብያ፣ ዝክሪ፤
ከሚያሚንና ከሞዓድያ፣ ፈልጣይ፤
18ከቢልጋ፣ ሳሙስ፤
ከሸማያ፣ ዮናታን፤
19ከዮያሪብ፣ መትናይ፤
ከዮዳኤ፣ ኦዚ፤
20ከሳላይ፣ ቃላይ፤
ከዓሞቅ፣ ዔቤር፤
21ከኬልቅያስ፣ ሐሸብያ፤
ከዮዳኤ፣ ናትናኤል።

22በኤሊያሴብ፣ በዮአዳ፣ በዮሐናንና በያዱአ ዘመን የሌዋውያኑ ቤተ ሰብ አለቆችና ካህናቱ፣ በፋርሳዊው በዳርዮስ ዘመነ መንግሥት ተመዝግበው ነበር። 23ከሌዋውያን ዘሮች መካከል እስከ ኤሊያሴብ ልጅ እስከ ዮሐናን ድረስ ያሉት የየቤተ ሰቡ ኀላፊዎች በታሪክ መጽሐፍ ተመዝግበው ነበር። 24የሌዋውያኑ መሪዎች ሐሸብያ፣ ሰራብያ፣ የቀድምኤል ልጅ ኢያሱ ነበሩ፤ እነርሱም ከወንድሞቻቸው ፊት ለፊት ሆነው የእግዚአብሔር ሰው ዳዊት በሰጠው መመሪያ መሠረት እየተቀባበሉ ውዳሴና ምስጋና ያቀርቡ ነበር።

25በቅጥሩ በሮች አጠገብ ያሉትን ዕቃ ቤቶች የሚጠብቁት ዘቦች ደግሞ መታንያ፣ በቅቡቅያ፣ አብድዩ፣ ሜሱላም፣ ጤልሞንና ዓቁብ ነበሩ። 26እነዚህም በኢዮሴዴቅ ልጅ፣ በኢያሱ ልጅ በዮአቂም፣ በአገረ ገዥ በነህምያ፣ በካህኑና በጸሓፊው በዕዝራ ዘመን አገለገሉ።

የኢየሩሳሌም ቅጥር ምረቃ በዓል

27የኢየሩሳሌም ቅጥር ሲመረቅ ሌዋውያኑ በምስጋና መዝሙር፣ በጸናጽል፣ በበገናና በመሰንቆ ድምፅ የምረቃውን በዓል በደስታ እንዲያከብሩ ከሚኖሩበት ተፈልገው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ። 28መዘምራኑንም እንደዚሁ በኢየሩሳሌም ዙሪያ ካለው ከነጦፋውያን መንደሮች በአንድነት ሰበሰቧቸው። 29በኢየሩሳሌም ዙሪያ የራሳቸውን መንደሮች ሠርተው ስለ ነበር፣ መዘምራኑን ያመጧቸው ከቤት ጌልገላ፣ ከጌባና ከዓዝምት አካባቢ ነው። 30ካህናቱና ሌዋውያኑ በሥርዐቱ መሠረት ራሳቸውን ካነጹ በኋላ፣ ሕዝቡን፣ ቅጥሩንና በሮቹን አነጹ።

31እኔም የይሁዳን መሪዎች በቅጥሩ ግንብ ዐናት ላይ እንዲወጡ
ወይም ከቅጥሩ ጎን እንዲሄዱ
አደረግሁ፤ ደግሞም ምስጋና እንዲያቀርቡ ሁለት ታላላቅ የመዘምራን ቡድን መደብሁ። አንዱ በቅጥሩ ግንብ ዐናት
ወይም ከቅጥሩ ጎን
በስተ ቀኝ በኩል “ቈሻሻ መጣያ በር” ወደሚባለው ሄደ።
32እነዚህንም ሆሻያና ከይሁዳ አለቆች እኩሌቶቹ ተከተሏቸው፤ 33የተከተሏቸውም ከዓዛርያስ፣ ከዕዝራ፣ ከሜሱላም፣ 34ከይሁዳ፣ ከብንያም፣ ከሸማያ፣ ከኤርምያስና፣ 35እንዲሁም መለከት ከያዙ ጥቂት ካህናትና ከአሳፍ ልጅ፣ ከዘኩር ልጅ፣ ከሚካያ ልጅ ከመታንያ ልጅ፣ ከሸማያ ልጅ፣ ከዮናታን ልጅ፣ ከዘካርያስ ጋር ነበር። 36ወንድሞቹ ሸማያ፣ ኤዝርኤል፣ ሚላላይ፣ ጊላላይ፣ መዓይ፣ ናትናኤል፣ ይሁዳና አናኒም የእግዚአብሔር ሰው ዳዊት ባዘዘው መሠረት የዜማ መሣሪያዎቹን ይዘው ሄዱ፤ ሰልፉን የሚመራውም ጸሓፊው ዕዝራ ነበረ። 37“ከምንጭ በር” ተነሥተው በቀጥታ ወደ “ዳዊት ከተማ” ደረጃዎች ወጡ፤ ከዚያም በቅጥሩ መውጫ በኩል አድርገው ከዳዊት ቤት በላይ በስተ ምሥራቅ ወደሚገኘው ወደ “ውሃ በር” ሄዱ።

38ሁለተኛው የመዘምራን ቡድን በስተ ግራ በኩል ሄደ፤ እኔም ከከፊሉ ሕዝብ ጋር ሆኜ በቅጥሩ ግንብ ላይ
ወይም ከቅጥሩ ጎን
፣ የእቶኑን ግንብ በማለፍ እስከ ሰፊው ቅጥር ተከተልኋቸው፤
39ከዚያም ከኤፍሬም በር በላይ፣ በአሮጌ በር
ወይም በጄሻና በር
፣ በዓሣ በር፣ በሐናንኤል ግንብ፣ በመቶዎቹ ግንብ ዐልፌ እስከ “በጎች በር” ድረስ ተከተልኋቸው። እነርሱም “በዘበኞች በር” አጠገብ ሲደርሱ ቆሙ።

40ቀጥሎም ምስጋና ያቀረቡት ሁለቱ የመዘምራን ቡድኖች፣ በእግዚአብሔር ቤት ቦታቸውን ያዙ፤ እኔም ከግማሾቹ ሹማምት ጋር ቦታዬን ያዝሁ፤ 41እንደዚሁም ካህናቱ ኤልያቄም፣ መዕሤያ፣ ሚንያሚን፣ ሚካያ፣ ኤልዮዔናይ፣ ዘካርያስና ሐናንያ መለከታቸውን ይዘው፣ 42መዕሤያ፣ ሸማያ፣ አልዓዛር፣ ኦዚ፣ ይሆሐናን፣ መልክያ፣ ኤላምና ኤጽር ቦታቸውን ያዙ፤ መዘምራኑ በይዝረሕያ መሪነት ዘመሩ። 43እግዚአብሔር ታላቅ ደስታ ስለ ሰጣቸው፣ በዚያች ዕለት ደስ ብሏቸው ብዙ መሥዋዕት አቀረቡ፤ ሴቶችና ልጆችም እንደዚሁ ደስ አላቸው፤ ከዚህም የተነሣ በኢየሩሳሌም የነበረው የደስታ ድምፅ እስከ ሩቅ ድረስ ይሰማ ነበር።

44በዚያን ቀን ስጦታው፣ በኵራቱና ዐሥራቱ የሚቀመጥበት ዕቃ ቤት የሚጠብቁ ሰዎች ተሾሙ። እነርሱም በየከተሞች ዙሪያ ከሚገኙት የዕርሻ ቦታዎች ሕጉ በሚያዝዘው መሠረት የካህናቱንና የሌዋውያኑን ድርሻ ወደ ዕቃ ቤቱ ማምጣት ነበረባቸው፤ ይሁዳ በሚያገለግሉ ካህናትና ሌዋውያን ደስ ተሰኝተው ነበርና። 45እንደ መዘምራኑና በር ጠባቂዎቹ ሁሉ፣ እነዚህም የአምላካቸውን አገልግሎትና የመንጻቱን ሥርዐት በዳዊትና በልጁ በሰሎሞን ትእዛዝ መሠረት ፈጸሙ። 46ቀድሞ በዳዊትና በአሳፍ ዘመን ለእግዚአብሔር የሚቀርቡትን የውዳሴ መዝሙሮችና ምስጋና የሚመሩ የመዘምራን አለቆች ነበሩ። 47በዘሩባቤልና በነህምያም ዘመን እስራኤል ሁሉ ለመዘምራኑና ለበር ጠባቂዎቹ የየዕለቱን ድርሻ ይሰጡ ነበር፤ የሌሎቹን ሌዋውያን ድርሻም ለብቻ ያስቀምጡ ነበር፤ ሌዋውያኑም ለአሮን ዘሮች ድርሻቸውን ያስቀምጡላቸው ነበር።

Copyright information for AmhNASV